ኢትዮጵያ፦ ወጣቱ ከብት አርቢ የተለያዩ ተግዳሮቶችን አልፎ በዶሮ ዕርባታ ስኬታማ ሆነ

| December 13, 2021

Download this story

ታዬ መርሳ የኢትዮጵያ ዋና ከተማ ከሆነችው አዲስ አበባ በ100 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በምትገኘው ወሊሶ ከተማ ነዋሪ ነው። ከዩኒቨርሲቲ ከተመረቀ በኋላ ነው ታዬ ወደ ዶሮ ዕርባታ ለመግባት የወሰነው። ነገር ግን እንደ ማንኛውም ስራ ፈጣሪ መሆን እንደሚፈልግ ወጣት አዲስ ተመራቂ ፈተናዎች አጋጥመውታል።  

ታዬ የዶሮ ዕርባታ ስራውን የጀመረው ኢቲዮ-ቺኪን ከተባለ ድርጅት ዶሮዎችን በመግዛት ነው። ታዬ በቤት ዶሮ ማርባት ሲጀምር ወላጆቹ ዕርባታው ግቢውን ማቆሸሹን እንዳልወደዱት በተደጋጋሚ ቅሬታቸውን ቢያሰሙም በስኬታማነት ዶሮዎቹን አራብቷል።

በሰፈር የሚደረጉ ዶሮ ዕርባታዎች ላይ በተለምዶ እንደሚታየው የታዬ ዶሮዎችም ሙሉ በሙሉ በሚባል ሁኔታ ምግባቸውን የሚያገኙት በፍለጋ ነው። እነዚህ ምግቦች ደግሞ በአብዛኛው የፕሮቲን፣ የሃይል ሰጪ ንጥረ ነገሮች እና የካልሲየም እጥረት ያለባቸው ሲሆን የእንቁላል ምርት ማሽቆልቆልን ያስከስታሉ። ጀማሪ እንደመሆኑ መጠን ታዬ ለዶሮዎቹ ገንቢ ንጥረ ነገር ይዘት ያለውን መኖ በመመገብ የርዶሮዎቹን የእንቁላል ምርት ከፍ ማድረግና በሽታ የመከላከል አቅማቸውን ማጎልበት እንደሚችል አልተረዳም ነበር።

ወጣት ታዬ በጓደኞቹ ታግዞ የተሻለ የዶሮ ማርቢያ ቤት ቢገነባም ለዶሮዎቹ ትክክለኛ መኖ እንዴት ሊያገኝ እንደሚችል ግንዛቤው አልነበረውም።  

ወደ ኋላ ሲያስታውስ “ የዶሮዎቼን ምርት ከፍ ሊያደርጉልኝ ስለሚችሉ አሰራሮች ዕውቀቱ አልነበረኝም። ስለ መኖዎች እና የአመጋገብ ስልቶች፣ በሽታዎች አንዲሁም የግብይት ስልቶች አላውቅም ነበር” ይላል።

ታዬ ተስፋ አልቆረጠም። አንድ ቀን የገበሬዎች ቡድን መሪ የሆነውን አጃኢብን ሲተዋወቅ መኖ እንዴት ማግኘት እንደሚችልና ገበያ እንዴት ማግኘት እንደሚችል ግንዛቤ ሊፈጥርለት ወደሚችለው ስልጠና ላይ በጋበዘው መሰረት ተገኝቶ ስልጠናውን ወሰደ። በስልጠናው ላይ ስለ አመርቂ ዶሮ እርባታ፣ ዶሮዎችን እና የዶሮ ምርቶችን ለመሸጥ አመቺውን ወቅት የቱ እንደሆነ የሚያስረዳ በርካታ ዕውቀት አገኘ። ስለ ትክክለኛ የዶሮ ማርቢያ ቤት አይነቶች፣ የዶሮ መኖ እና የዶሮ ጤና አጠባበቅ ተምሯል።  በየሳምንቱ የዶሮ ማርቢያ ቤቶችን በደንብ የማጽዳቱን አስፈላጊነት እንዲሁም ለዶሮዎቹ በቂ ንጹህ ውሃ የማቅረብን አስፈላጊነትም  በተጨማሪ ተረድቷል።

በመጨረሻም ዶሮዎቹን በየጊዜው ማስከተብ እንደሚያስፈልግ እና የዶሮዎቹ ብዛት ከሚያቀርብላቸው ምግብ እና ቦታ ስፋት ጋር መዛመድ እንዳለበት ተገንዝቧል።

 “ጥሩ የኤክስቴንሽን አቀራረብ እና ስልጠናዎች የዶሮ ምርትን እና ምርታማነትን ለማሻሻል ከሚጠቅሙት ሁለቱ ግብአቶች መሃል ናቸው። የኤክስቴንሽን አቀራረብ እና ስልጠናዎች  ስርአቱን ለማሻሻል ሲባል በባለሙያዎች መቅረብ ያለባቸው ሲሆን ተከታታይ ግምገማ እና ማሻሻያም ያስፈልጋቸዋል” ይላል ወጣት ታዬ።

እንዲህ ያለው ሥልጠና ዘርን ስለ መምረጥ፣ የዶሮ ማራቢያ ቤት፣ የዶሮ አመጋገብ፣ አስተዳደር፣ በሽታን መቆጣጠር እና በመንደር ውስጥ ለሚደረጉ የእርባታ ስርዓት ውስጥ ያሉ የባዮሴኪዩሪቲ መረጃዎችን ማካተት እንዳለበትም አክሏል።

የስልጠና እና የኤክስቴንሽን ምክሩ የዶሮ ዝርያ እና ወቅትን ያገናዘበ ካልሆነ ስኬታማ ለመሆን አስቸጋሪ እንደሚሆን ታዬ ይናገራል።

በጓደኞቹ ድጋፍና ምክር ታግዞ የንግድ ዕቅድ በመንደፍ ታዬ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ብድር ተቀብሏል። በብድሩ 100 ንብርብር እና 100 ዶሮዎችን ለመግዛት የቻለ ሲሆን በየጊዜው አክሲዮኑን ከማሳደግ በተጨማሪ ጥሩ የሚባል ገቢ ያገኛል።

አቅርቦቶቹን ወደ ገቢያ ለማመላለስ ያስችለው ዘንድ ከጀርባው መጫኛ ያለው ሞተር ሳይክል ገዝቷል።

ዛሬ ላይ የወጣት ታዬ የዶሮ እርባታ ቤት በፀሃይ ሃይል የሚሰራ ሲሆን ገሚሱ የጣራው ክፍል ተሸፍኗል። በተጨማሪም ሌሎች በርካታ ፕሮጄክቶችን በማስተዳደር ላይ ይገኛል።

በማጠቃለል ታዬ እንዲህ ይላል፡- “በህይወቱ ላይ ለውጥ የሚፈልግ ማንኛውም ሰው በአነስተኛ ገንዘብ ቀላል ስራ መጀመር ይችላል። ገቢ ለማግኘት ጥሩ የንግድ እቅድ፣ የቴክኒክ ድጋፍና ስልጠና ያስፈልጋል። የሚያስፈልገው ብቸኛው ነገር ተነሳሽነት እና ቁርጠኝነት ነው። በተለይ በዶሮ እርባታ ስራ እኔን እንደ ተምሳሌት መውሰድ ይቻላል። የምን ጊዜም መፈክሬ ‘ጠንክሮ መስራት ስኬትን ያስገኛል!’ ነው።”

ይህ ግብአት በኢትዮጵያ የዶሮ እርባታን ማሳደግ የተሰኘው ሬዲዮ ፕሮግራም አካል በሆነው አይ.ኤፍ.ሲ የገንዘብ ድጋፍ የተከናወነ ነው።