ኢትየፐጵያ: የቦቆሎ አርሶ አደሮች ፈጣን ሁሉን አውዳሚ ተምችን ለመቆጣጠር ልዩ ዛፎችን ያበቅላሉ

| November 14, 2022

Download this story

News Brief

ሀርቤ ታፈሰ በደቡብ ኢትዮጵያ ዶሬ ባፌኖ አውራጃ በቆሎ ወደ ሚያመርተው 625 ካሬ ሜትር ቦታ በጠባብ መተላለፊያ መንገድ ትሄዳለች። Fall Armyworm ለማስተዳደር ፑሽ-ፑል የሚባል ዘዴ ትጠቀማለች። ዘዴው በሁለት መንገዶች ይሠራል. በመጀመሪያ የዴስሞዲየም ዘርን በበቆሎ መደዳዎች መካከል መትከል የፎል Armyworm እና ሌሎች ተባዮችን ያስወግዳል። በሁለተኛ ደረጃ በበቆሎ እርሻው ድንበር ዙሪያ ብራቺያሪያን መትከል ተባዮቹን ከበቆሎዋ ላይ ይስባል ወይም ይጎትታል። ይህ ለአካባቢ ጥበቃ ተስማሚ የሆነ የተባይ ማጥፊያ ዘዴ የበቆሎ ግንድ አሰልቺን በመቆጣጠር ረገድም ውጤታማ ነው።

ሀርቤ ታፈሰ በደመናማው ጠዋት በመኖሪያዋ በኩል ያለውን ቀጭን መንገድ ይዛ የ625 ካሬ ሜ. ስፋት ወዳለው የቦቆሎ ማሳዋ እየገሰገሰች ነው፡፡ የስድስት ልጆች እናት የሆነችው ሀርቤ ማሳዋ በኣካባቢው በቅርቡ ከተከሰተው የፈጣን ሁሉን አውዳሚ ተምች ወረራ ነፃ መሆኑን ለማረጋገጥ ዛሬም ማልዳ ገስግሳለች፡፡

ወይዘሮ ሀርቤ በደቡብ ኢትዮጵያ የዶሬ ባፈኖ ወረዳ ኗሪ ነች፡፡ የፈጣን ሁሉን አውዳሚ ተምችን ለመቆጣጠር እየተጠቀመች ያለችው መሳብ እና መግፋት “push-pull” የተሰኘ ዘዴን ነው፡፡ ቦቆሎን በምትዘራበት ወቅት ቦቆሎ ሰብሎቿ ላይ የሚያርፉ የተምቾችን ቁጥር ለመቀነስ የሚረዷት እና በዴዝሞዲየም እና ብራቺያራ (Desmodium and Brachiaria) የተሰኙ ዛፎችን ታሰባጥራለች፡፡

እንደ ወይዘሮዋ አባባል ዴዝሞዲየም ተምቾችን በሽታቸው የመግፋት (የማባረር ሀይል አላቸው፡፡) በአንፃሩ ብራቺያራ ደግሞ ተምቾችን ባለው ሽታ ይስባቸዋል፡፡ ሀርቤ “ ይህ ዘዴ ተምቾችን የቦቆሎ ሰብሎቿ ላይ እንዳያርፉ በማድረግ ሰብልን ከጉዳት ለመታደግ በእጅጉ ረድቶኛል፡፡ የእኔ ብቻ አይደለም ከእኔ ቀጥሎ ያለው ማሳ ጭምር ከፈጠን ሁሉን አውዳሚ ተምች ነፃ የሆነ ይመስለኛል ” ስትልም ገልፃልናለች፡፡

ይህ ዘዴ በሁለት መንገድ ይሰራል፡፡ በመጀመሪያ የዴዝሞዲየም ዘር በቦቆሎ ሰብል መደዳ መካከል ማብቀል ፈጣን ሁሉን አውዳሚውን እና ሌሎች ተምቾችን ይገፋቸዋል፤በመቀጠል ብራቺያራ በቦቆሎ ማሳ ዙሪያ ማብቀል ተምቾቹን ከማሳዋ እየሳበ ወደ ቦቆሎ ሰብሏ እንዳይሄዱ ያደርግላታል፡፡

በአካባቢዋ የሚገኙ በርካታ አርሶ አደሮችም የቦቆሎ ሰብሎቻቸውን ከፈጣን ሁሉን አውዳሚ እና ሌሎች ተምቾችን ለመከላከል ይህንኑ ዘዴ በመጠቀም ይገኛሉ፡፡

ወይዘሮ ሀርቤ የቦቆሎ ማሳዋ ላይ ደርሳ የምትጠቀምበት የስበት እና የመግፋት ዘዴዋ ማሳዋን እስካሁን ከጉዳት እየተከላከለላት መሆኑን በማረጋገጥ እፎይ ብላለች፡፡ ሀርቤ “በመጀመሪያ ባለፈው ዓመት ነበር የስበት እና የመግፋት ዘዴን የተገበርኩት፡፡ ፍላጎቴ ቦቆሎዬን ከአገዳ ቆርቁር ለመከላከል ነበር ሆኖም ግን ዘዴው ፈጣን ሁሉን አውዳሚውን እና ሌሎች ተባዮችን ለመከላከል ጭምር ውጤታማ መሆኑን አረጋገጥኩኝ፡፡” ብላናለች፡፡

በዶሬ ባፈኖ ወረዳ ያሉ ሁሉም አርሶ አደሮች የስበት እና የመግፋት ዘዴን አልተዋወቁትም፡፡ ወይዘሮ ሀርቤ ዘዴው ስላለው ጥቅም በአካባቢዋ ላሉ አርሶ አደሮች ለማሳወቅ እየጣረች መሆንዋን ገልፃልናለች፡፡

በመቀጠልም : “በዚህ ዓመት ዘዴውን እንዲተገብሩት በሚል ከማሳዬ ነቅዬ ለሶስት አርሶ አደሮች አካፍያለሁ ፤ እነሱም በየማሳዎቻቸው ተክለዉት ውጤቱንም ለሌሎች እየመሰከሩ ነው፡፡ ከዚያም አልፈው ዘዴውን እንዴት መጠቀም እንዳለባቸው ሌሎች አርሶ አደሮችን እያስረዱ የገኛሉ፡፡” ስትል ተመኩሮዋን ገልፃለች፡፡

ሽኩሬኪትሳም በዶሬ ባፈኖ ወረዳ የሚኖር እና ዘዴውን የሚተገብር ሌላ አርሶ አደር ነው፡፡ አርሶአደሩ : “የስበት እና የመግፋት ከመተግበሬ በፊት ከማበቅለው ከዘህ ቀደም ከማገኘው 2000 ኪሎ ግራም ቦቆሎ ውስጥ 500 ኪሎ ግራም የሚደርሰውን በተምቾች ሳቢያ እያጣሁ ነበር፡፡ የስበት እና የመግፋት ዘዴን በእያንዳንዱ የአርሶ አደር የቦቆሎ ማሳ ላይ መተግበር ከተቻለ ፈጣን ሁሉን አውዳሚ ተምችን በበቂ ሁኔታ መቋቋም እንችላለን ” ሲል አክሎ ገልፆልናል፡፡

ባዩ እንቻለው በኢንተርናሽናል ሴንተር ኦፍ ኢንሴክት ፊዚዮሎጂ ኤንድ ኢኮሎጂ (International Centre of Insect Physiology and Ecology ICIPE) የመስክ ረዳት ነው፡፡ የስራ አጋሮቻቸው የስበትን እና የመግፋት ዘዴን ከአካባቢ ጥበቃ አኳያ የግንደ ቦርቡር ተምችን ለመከላከል አቅደው ለኢትዮጵያ አርሶ አደሮች አስተዋውቀዋል፡፡ ኋላ ላይ ግን ዘዴው ፈጣን ሁሉን አውዳሚ ተምችንም የመከላከል ብቃት እንዳለው ለማረጋገጥ ተችሏል፡፡

ይህ በ ዩ ኤስ ኤ አይ ዲ ፊድ ዘ ፊውቸር ኢትዮጵያ ቫልዩ ቼይን አክቲቪቲ እንደ ፕሮጀክቱ አካል በመሆን ባደረገው ድጋፍ የተዘጋጀ ነው፡፡ “ICT-enabled Radio Programming on Fall Armyworm (FAWET).

ፎቶ፡- ሀርቤ ታፈሰ በበቆሎ ማሳዋ። ክሬዲት: ኒዮ ብራውን.

ይህ ታሪክ በመጀመሪያ በነሐሴ 6፣ 2018 ታትሟል።