ተባይ መከላከያ ኬሚካልን በጥንቃቄ መጠቀም፡የአዲሱ ተምች ሁኔታ በኢትዮጵያ

| November 13, 2019

Download this story

ማስታወሻ ለአዘጋጆች

በሳብ ሰሃራን አፍሪካ የሚገኙ ቦቆሎ አምራች አርሶ አደሮች ፈጣን ሁሉን አውዳሚ ተምች እና ሌሎች ተምቾች ሰብሎቻቸው ላይ የሚያደርሱትን ጉዳት ለመከላከል የተለያዩ ዘዴዎችን እየተጠቀሙ በመሞከር ላይ ናቸው፡፡ ፈጣን ሁሉን አውዳሚ ተምች በዋናነት ቦቆሎን የሚመገብ እና ከቦታ ቦታ በፍጥነት የሚሰደድ የተምች ዓይነት ነው፡፡ በአፍሪካ ከተከሰተበት ከ2016 ጀምሮ በአፍሪካ ምድር ከአርባ በላይ በሚደርሱ አገራት የቦቆሎ ምርት ላይ ቀላል የማይባል ጉዳት አድርሷል፡፡ ባለሙያዎችም ተምቹ በዚህ መልኩ የሚቆይ ዓይነት እደሆነ ነው ሚገልፁት፡፡

በኢትዮጵያም ከግማሽ የሚበልጠው ማለትም ከ55 ሚልየን በላይ የሚደርስ ህዝብ ቦቆሎን ለምግብነትም ለገቢ ምንጭነትም ያመርታል፡፡ በገጠራማዎቹ ስፍራዎች 1/5ኛ የካሎሪ ልኬታቸውን የሚያገኙት ከቦቆሎ ምርት ነው፡፡

አርሶ አደሮች የሳት እራቶችን ከሰብሎቻቸው ላይ በእጆቻቸው በመልቀም ያስወግዳሉ፡፡ የፀረ ተባይ መድሃኒቶችን ከአካባቢ ሰብሎች ውጭ በማዘጋጀት እና ሰብሎቻቸውን ጤናማ እና ፈጣን ሁሉን አውዳሚው ተምችን ለመቋቋም እንዲችሉ የሚችሉትን ሁሉ በማድረግ ላይ ናቸው፡፡ ነገር ግን እነዚህ ዘዴዎች በቂ ሳይሆኑ ሲቀሩ ኬሚካል ፀረ ተባይም ሌላው ውጤታማ አማራጭ ዘዴ ይሆናል፡፡

ሆኖም ግን የኬሚካል ፀረተባዮች ከጤና አኳያ ለአርሶ አደሮች፣ ለቤተሰቦቻቸው፣ ለአካባቢው፤ ምርቱን በምግብነት በሚጠቀሙ ሰዎች እና ፈጣን ሁሉን አውዳሚ ተምች የሚያጠቁት ተፈጥሮአዊ ጠላቶችን ጭምር ሊጎዳ ይችላል፡፡

ይህ ፅሁፍም ኬሚካሎችን በተቻለ መጠን በፀረ ተባይነት ከመጠቀም መቆጠብ በሚኖረው አስፈላጊነት እንዲሁም አርሶ አደሮች ሊያደርጓቸው በሚገቡ ዝርዝር ተግባራት እና ሊያሟሏቸው በሚገቡ ጉዳዮች ላይ ያተኩራል፡፡ ይህም ኬሚካል ጸረ ተባዮችን መቼ እና እንዴት መጠቀም እዳለባቸው፤ ግብአቶችን እንዴት ማስቀመጥ እና ማፅዳት እንደሚገባ፤ እንዲሁም የመከላከያ አልባሳት አጠቃቀም ጭምር ያካትታል፡፡ እነዚህ መረጃዎች አርሶ አደሮች እንዴት ራሳቸውን፣ቤተሰቦቻቸውን እና ማህበረሰባቸውን ከጉዳት መከላከል እንደሚችሉ ለማስገንዘብ ይረዳል፡፡

እንደ አዘጋጅ አንቺ ወይም ባልደረባሽ በሬድዮ ፕሮግራማችሁ ላይ ልታነቡት ትችላላችሁ፡፡ ወይም ደግሞ ስልክ በመደወል ፤ የፅሁፍ መልዕክት በመላክ አልያም ዕውቀቱ ያለው አርሶ አደርን በመጋበዝ በቃለ መጠይቅ መልኩ ለሚዘጋጅ የሬድዮ ፕሮግራማችሁ መረጃውን እንደ መነሻ በማድረግ ልትጠቀሙበት ትችላላችሁ፡፡ ይህ ፅሁፍ በተለይ በቆሎ አምራች ለሆኑ እና ፈጣን ሁሉን አውዳሚ ተምች ቁጥጥር ላይ ላሉ ኢትዮጵያውያን አርሶ አደሮች የተዘጋጀ ሲሆን ምክሩ ለሌሎች አፍሪካውያንም ጠቃሚ ነው፡፡ በኬሚካል አጠቃቀም ደህንነት ዙሪያ የሚሰጡት ሀሳቦች ሁሉም ፀረ ተባይ ኬሚካል ተጠቃሚዎች ሊተገብሩት ይችላሉ፡፡

ይህንን ፅሁፍ እንደ እንደ አንድ የፅሁፋችሁ የጥናት አካል አድርጋችሁ ወይም ለቃለ መጠይቅ የሚሆኑ ጥያቄዎች ለማዘጋጀት የምትጠቀሙበት ከሆነ የሚከተሉትን ነጥቦች ታሳቢ ማድረግ ይኖርባችኋል:-
• በአካባቢያችሁ አርሶ አደሮች ፈጣን ሁሉን አውዳሚ ተምችን ለመከላከል ከፀረ ተባይ ኬሚካል ውጭ የሚተገብሯቸው ዘዴዎች ምን ምን ናቸው ?
• አርሶ አደሮች ፀረ ተባይ ኬሚካሎችን ለመርጨት የሚያስችሏቸው ራሳቸውን የሚከለከሉባቸውን ግብአቶች የሚያገኙት ከየት ነው? የሰለጠኑ የፀረ ተባይ ኬሚካል የሚረጩ ባለሙያዎች በአካባቢያችሁ አሉ?
• ፈጣን ሁሉን አውዳሚ ተምችን ለመከላከል ፀረ ተባይ ኬሚካልን ምርጫቸው ያደረጉ የአካባቢያችሁ አርሶ አደሮች ከደረሱባቸው ጉዳቶች ጥቂቶቹ ምንድናቸው ?

ሊይዘው የሚችለው የአየር ሰዓት:-ከ መግቢያ ድምፅ እና ከመሸጋገሪያ ሙዚቃ ውጭ 20-25 ደቂቃዎች

http://scripts.farmradio.fm/am/radio-resource-packs/109-farm-radio-resource-pack-amharic-oromifa/using-chemical-pesticides-safely-amharic/