Fanta Kando | March 25, 2024
News Brief
ዌንድያም ሳዋዶጎ ከ 2015 ጀምሮ ከሲቪል መሐንዲስ ባለቤቷ ጋር ሥራን እና የቤት ውስጥ ሕይወትን በብቃት ሚዛናዊ ያደረገች በኡጋዱጉ ፣ ቡርኪናፋሶ ውስጥ በሥራ አስፈፃሚ ረዳትነት የምትሰራ ሴት ነች። ሶስት ልጆች አሏቸው። የቤት ውስጥ ኃላፊነቶችን ይጋራሉ፡- ማድ ቤቱ የእርሷ ኃላፊነት ነው፣ እሱ ልጆቹን መንከባከብ እና የመላላክ ስራዎችን ይሰራል። ግብይትን ደግሞ አብረው ይከውናሉ። ተባብሮ የመስራት ስልታቸው የተሻሻለው ወይዘሮ ሳዋዶጎ በ2019 ሥራ መሥራት ከጀመረች በኋላ ነው። ስልታቸው ትብብርን አፅንዖት ሰጥቷል እና የቤት ሰራተኛ መቅጠርንም ያካትታል። ሳዋዶጎዎች በጋራ መግባባት እና ልጆቻቸውን የቤት ውስጥ ስራዎችን የመጋራት ዋጋ በማስተማር ላይ ያተኩራሉ።
በዲሴምበር — የስራ ቀን መጨረሻ ሰኞ ከምሽቱ 5 ሰአት ላይ ነው። ከስኬታማ ቀን በኋላ፣ ስራ አስፈፃሚዋ ዌንድያም ሳዋዶጎ ከኦጋዱጉ፣ ቡርኪናፋሶ በስተሰሜን በሚገኘው ባሲንኮ ሰፈር ወዳለው ቤቷ ተመለሰች። አሁን አንዳንድ የቤት ውስጥ ስራዎችን በባለቤቷ ድጋፍ መሥራት ትችላለች። እንደ እሷ አገላለጽ፡- “ከስራ በኋላ የማድ ቤቱን ስራ እሰራለሁ፣ ባለቤቴ ደግሞ ልጆቹን ከትምህርት ቤት ያመጣል።”
የሳዋዶጎ ጥንዶች ለቤተሰባቸው ደህንነት ሲባል የቤት ውስጥ ሥራዎችን ለመካፈል መርጠዋል። ከ2015 ጀምሮ በትዳር ውስጥ ኖረዋል እናም ሶስት ልጆች አፍርተዋል። ወይዘሮ ሳዋዶጎ በኢንሹራንስ ዘርፍ ትሰራለች፣ አቶ ሳዋዶጎ በህዝብ አስተዳደር ውስጥ ሲቪል መሐንዲስ ነው። ወይዘሮ ሳዋዶጎ የቤት ውስጥ ሥራዎችን ብቻ ትሰራ ነበር፣ ነገር ግን በ2019 ከአገር ውስጥ የኢንሹራንስ ኩባንያ ጋር መሥራት ጀመረች። ከአዲሱ ኃላፊነቷ የተነሳ የቤት ውስጥ ስራዎችን ከባለቤቷ ጋር እንዴት መካፈል እንዳለባት ትናገራለች።
ያን በተመለከተ ወይዘሮ ሳዋዶጎ እንደዚህ ትላለች:- “ለባለቤቴ ግንዛቤ ምስጋና ይግባውና የቤት ውስጥ ሥራዎችን እንደገና ተከፋፍለናል። ሙያዊ ስራዬን ማጎልበት እና እንደ ሚስት እና እናት ያለኝን ሚና ሙሉ በሙሉ መጫወት እችላለሁ።”
አቶ ሳዋዶጎ ሚስቱ የቢሮ ሥራዋን እየሰራች የቤት ውስጥ ሥራዎችን ብቻዋን ማስተዳደር እንደማትችል አምኗል። እሱም ያብራራል:- “ሁሉንም የዕለት ተዕለት ተግባራት ለይተናል፣ እናም የእያንዳንዱን ሰው ሚና በገባነው ቃል መሰረት ወስነናል።” ልጆቹን እና ለቤተሰቡ ሌሎች ከቤት ውጪ ያሉ የዕለት ተዕለት እንቅስቃሴዎች የሱ ሀላፊነት ናቸው፣ ሚስቱ ደግሞ ምግብ ማብሰል ላይ ታተኩራለች። አክሎም:- “የቤት ውስጥ ሥራዎችን በተመለከተ፣ በተቻለ መጠን እረዳታለሁ፣ አንዳንድ ጊዜ የግብይት ሥራዎችን አብረን እንሰራለን።”
በጋራ ከመደጋገፍ በተጨማሪ የሳዋዶጎ ጥንዶች የቤት ሰራተኛ ቀጥረዋል። ረጅም ጉዞዎችን ለማስቀረትም ልጆቻቸውን በቤት አቅራቢያ በሚገኙ ትምህርት ቤቶች ለማስመዝገብ ወስነዋል።
ብሌዝ ቲዬኒን በቡርኪናፋሶ የህዝብ አገልግሎት የሥርዓተ-ፆታ እኩልነት ኤክስፐርት ነው። የሀገሪቱ የቤተሰብ ህግ እያንዳንዱ የትዳር ጓደኛ ያለ ሌላኛው ፍቃድ በሚፈልገው የሙያ መስክ ላይ እንዲሰመራ የሚፈቅድ ሲሆን ይህም የቤተሰቡን ጥቅም አደጋ ላይ የሚጥል ካልሆነ በስተቀር ነው ብሏል። እንደ አቶ ቲዬኒን ገለጻ፣ ባለትዳሮች የቤት ውስጥ ሥራዎችን ጨምሮ ቤተሰቡን እንዲያስተዳድሩ የመረዳዳት ግዴታ አለባቸው። ይህንን በተመለከተ አቶ ብሌዝ ቲዬኒን እንዲህ ይላል፡- “ባሎች ሚስቶቻቸውን በቤት ውስጥ ስራ መርዳት አለባቸው በክፍያ የሚሰራ ስራ ለመስራት እና የግል ህልሞቻቸውን ለማሳካት ጊዜ እንዲኖራቸው።” ይህም ሴቶች ገቢ እንዲያገኙ እና ቤተሰቡን በብቃት እንዲያስተዳድሩ ያስችላቸዋል።
አቶ ሳዋዶጎ የባለቤቱ ሥራ ለቤተሰቡ ደህንነት ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንደሚያበረክት እና ገቢዋ የቤተሰብ ፍላጎቶችን ለማሟላት እንደሚረዳ ይናገራል። ወይዘሮ ሳዋዶጎም ተመሳሳይ ስሜት እንዳላት ትናገራለች:-“ይህ ስራ እንዳድግ ያስችለኛል። አነስተኛ ፍላጎቶቼን ማሟላት እና ባለቤቴን በፕሮጀክቶቹ መደገፍም እችላለሁ።”
ወይዘሮ ሳዋዶጎ የአጋርነታቸው ስኬት ምስጢር በእሷ እና በባለቤቷ መካከል ባለው ቅንጅት፣ ውይይት እና መግባባት ላይ የተመሰረተ ነው ትላለች። በወደፊት ትውልዶች ውስጥ ይህንን ስኬት ለማስቀጠል ልጆች በቤተሰብ ውስጥ ተግባራትን የመጋራት አስፈላጊነትን መማር አለባቸው ብላ ታምናለች። አቶ ቲዬኒንም በዚህ ሃሳብ ይስማማል ፣ እናም ጾታን ያማከለ የልጆች አስተዳደግን አስፈላጊነት በተመለከተ በቤተሰብ ውስጥ ፍትህን እና ፍትሃዊነትን በማስተዋወቅ ፣ ለሴቶች እና ለወንዶች እኩል እድል በመስጠት ፣ ከሥርዓተ-ፆታ ልዩነት አድልኦ የፀዳ ፍትሃዊ ማህበረሰብ በመገንባት እና ወደ አካታች እና ዘላቂ ልማት ለመሸጋገር ያለውን ጠቀሜታ አፅንዖት በመስጠት ይናገራል።
አቶ ቲዬኒን ሲያጠቃልል ወላጆች የቤት ውስጥ ሥራዎችን እና ስራዎቹን የሚያከናውኑትን እንዲያደንቁ እና በሴቶች እና በወንዶች መካከል ፍትሃዊ በሆነ መንገድ ማከፋፈል ላይ ትኩረት እንዲሰጡ በመምከር ይህም የሚሳካው እያንዳንዱ ሰው በራሱ መንገድ ለቤተሰቡ ደህንነት አስተዋጽኦ እንዲያደርግ በማረጋገጥ ነው ይላል። ወይዘሮ ሳዋዶጎ በባለቤቷ ድጋፍ መደሰቷን ገልጻ:- “ በቤተሰቤ ረክቻለሁ እናም ደስተኛ ነኝ!”
ይህ ጽሑፍ የተዘጋጀው በ‘ዩኬር– አንፔይድ ኬር ከሰሃራ በታች ባሉ የአፍሪካ ሀገራት‘ ተነሳሽነት ሲሆን ይህም የፆታ እኩልነትን እና የሴቶችን አቅም ለማሳደግ ያለመ በቤተሰብ እና በቤተሰብ ውስጥ ያለ ያለ ክፍያ የሚሰራ የእንክብካቤ እና የቤት ውስጥ ስራ ተገቢ እና ፍትሃዊ በሆነ መልኩ ለመጋራት ቁርጠኝነት ነው። – ከሰሃራ በታች ባሉ የአፍሪካ. ሀገራት ፕሮጀክቱ ከግሎባል አፌርስ ካናዳ በተገኘ የገንዘብ ድጋፍ ከፋርም ራዲዮ ኢንተርናሽናል (FRI)፣ የተባበሩት መንግስታት የሴቶች ቢሮ እና እና ዘ አፍሪካን ዊሜንስ ደቨሎፕመንት ኤንድ ኮሚኒኬሽንስ ኔትወርክ (FEMNET) ጋር በመተባበር ይተገበራል።