• enEnglish
  • frFrançais
  • ptPortuguese
  • swSwahili
  • amAmharic
  • haHausa
  • Stories
  • Resources
  • Script of the week
  • Opportunities
  • Spotlights
  • FRI in Action
  • This story is also available in English
  • This story is also available in Français
  • This story is also available in Swahili

Tanzania:- ኮቪድ-19 ሴቶች ነጋዴዎችን በአዲስ መልክ እንዲሸጡ አስገድዷቸዋል (በኢኖስ ሉፉንጉሎ)

Enos Lufungulo | June 10, 2020

amharic-post_tag emergencies-am markets

Share this:

  • Facebook
  • X

Download this story

News Brief

Marketplaces are typically bustling and busy, but as people try to protect themselves from the coronavirus, they are avoiding crowded places. This affects female vendors, who are now trying to sell new products or sell in new ways. In Tanzania’s Moshi district, Sophia Kimaro relied on selling vegetables and fruit. But since clients are avoiding marketplaces, she has changed her business model. She now sells snacks to local buyers, receiving orders by phone. She explains that products like bananas, avocados, and oranges are available at many homes in the area, but almost every family needs mandazi and vitumbua for breakfast. Phone orders and motorcycle delivery are helping keep businesses alive, but this is a new way of operating for both vendors and customers—and it’s not without challenges.

ሰዓቱ መሽቷል፣ ዝናብም እዘነበ ነው፡፡ ሶፍያ ኪማሮ ግን ነገ ጧት ለምትጋግረው ቦምቦሊኖ እና የሩዝ ቂጣ የስንዴ እና ሩዝ ዱቄት በማዘጋጀት ተጠምዳለች፡፡ “አስራ አንድ ሰዓት ከእንቅልፌ ተነስቼ እጋግራለሁ፡፡ ከአንድ እስከ ሦስት ሰዓት ደግሞ ለደምበኞቼ በየቤታቸው እየወሰድኩ እሸጥላቸዋለሁ፡፡ አንዳንድ ሰዎች ቤቴ መጥተው ይገዛሉ፣ ሌሎች ደግሞ በስልክ ያዙኛል” ትላለች፡፡

ወይዘሮ ኪማሮ በሰሜናዊ ታንዛንያ ኪሊማንጃሮ ክልል ሞሺ በሚባል አካባቢ ትኖራለች፡፡ ገቢ የምታገኘው በዋናነት እህል ወደ ገበያ ወስዳ በመሸጥ ነው፡፡ ኮሮናቫረስ ገበያውን ካቋረጠው በኋላ ግን የንግድ ሥራዋን መቀየር ነበረባት፡፡ ሰዎች ገበያ ቢወጡ በሽታው የሚይዛቸው እየመሰላቸው ይፈራሉ፡፡ አሁን ገቢ የምታገኘው ቦምቦሊኖ እና የሩዝ ቂጣ በመሸጥ ነው፡፡

እንዲህ ትላለች፡- “ደምበኞች ከገበያ መጥተው የሚገዙትን አትክልት፣ ሙዝ፣ አቮካዶ፣ ብርቱካን እና ድንች ብቻ ተማምኖ ከመቀመጥ ሥራየን ለመቀየር ወስኛለሁ፡፡ በኛ አካባቢ እነዚህ ምርቶች ብዙ ሰዎች ቤት ውስጥ ይገኛሉ፤ ግን ሁሉም ቤተሰብ ለቁርስ ቦምቦሊኖ እና የሩዝ ቂጣ ይፈልጋል፡፡”

አክላም እንዲህ ትላለች፡- “ለአዲሱ ሥራዬ በኮቪድ-19 ምክንያት ወደ ገበያ አልሄድም፡፡ ቦምቦሊኖ እና የሩዝ ቂጣ የምሸጠው ከቤቴ ሆኜ ነው፡፡”

ይህ የሥራ ለውጥ ገቢዋን በጣም እንደቀነሰባት ወይዘሮ ኪማሮ እንዲህ ታስረዳለች፡፡ “ገበያ ስሄድ በወር ከ100,000 to 130,000 የታንዛንያ ሽልንግ (ከ43-56 የአሜሪካ ዶላር) አተርፍ ነበር፤ አሁን ግን ትርፌ በወር ከ40,000 እስከ 60,000 የታንዛንያ ሽልንግ (ከ17-26 የአሜሪካ ዶላር) ነው፡፡”

ግሬስ ጆን አሩሻ ከተማ ባላት ስጋ ቤት ስጋ፣ አሳ፣ እንቁላል እና ሌሎች የእንስሳት ተዋጽኦዎች ትሸጣለች፡፡ ነገር ግን ኮቪድ-19 የእሷንም ሥራ አላተረፈላትም፡፡ “በኮቪድ-19 ምክንያት ሥራዬ ተንኮታኩቷል፡፡ በሽታውን በመፍራት የደምበኞቼ ቁጥር ቀንሷል” ትላለች፡፡

አክላም እንዲህ ትላለች፡- “አሁንም ሥራዬን እየሠራሁ ነው፣ ግን በተለየ መንገድ፡፡ በስጋ ቤቴ ውስጥ ከመሸጥ ይልቅ ቤት ለቤት አስረክባለሁ፡፡ ደምበኞች ቴክስት በማድረግ ወይም በመደወል ያዙኛል፡፡ ከዚይ ትእዛዛቸውን በሞተር ሳይክል እልክላቸዋለሁ፡፡”

ቤት ለቤት በማስረከብ መሥራት ብዙ ተግዳሮቶች ሲኖሩት ገቢዋንም እንደቀነሰባት ወይዘሮ ጆን ትናገራለች፡፡ “ይሄ አዲስ ዓይነት አሻሻጥ ስለሆነ ብዙ ሰዎች ገና አልለመዱትም፡፡ በመሆኑም የማስረከቢያ ክፍያውን ብዙ ሰዎች አቅማቸው ስለማይፈቅድ የደምበኞች ቁጥር ቀንሷል፡፡”

ጄን እንጋሳ በታንዛንያ በእምፓንዳ ዲስትሪክት እንሴምልዋ መንደር የምትኖር ነጋዴ ናት፡፡ ኮቪድ-19 የሷንም ሥራ ጎድቶባታል፡፡ “ዕቃ የምንሸጥበት ገበያ የለም፣ ዕቃ የሚገዛም በቂ ደምበኛ የለም፡፡”

ወይዘሪት እንጋሳ በቆሎ፣ ባቄላ፣ እና ሩዝ የመሳሰሉ የምግብ እህሎችን ለቸርቻሪዎች ታከፋፍልና ወደ ሌሎች የታንዛንያ ክፍሎችም ትልክ ነበር፡፡ ያ ሁሉ በኮቪድ-19 ምክንያት ቆሟል፡፡

“አሁን ወደ ሌሎች የሃገሪቱ ክፍሎች አልልክም፣ ምክንቱያቱም በዚያ ያሉ ደምበኞቼም ሥራ ወድቋል፡፡ አሁን ከኔ ለመግዛት ለመጀመር ዝግጁ አይደሉም፡፡”

ወይዘሪት እንጋሳ ቀጥላም እንዲህ ትላለች፡- “ቤቴ መጥተው ለሚገዙ ደምበኞች ብቻ እሸጣለሁ፡፡ ደስ የሚል ሁኔታ አይደለም፤ መቼ እንደሚስተካከልም አላውቅም፡፡ በወር እስከ 350,000 የታንዛንያ ሽልንግ (150 የአሜሪካ ዶላር) ትርፍ አገኝ ነበር፡፡ አሁን 70,000 የታንዛንያ ሽልንግ (30 የአሜሪካ ዶላር) ብቻ አገኛለሁ፡፡

ኮቪድ-19 የነጋዴዎችን አሠራር ብቻ ሳይሆን አኗኗራችውንም ጭምር ነው የቀየረው፡፡ ወይዘሪት እንጋሳ እንዲህ ትላለች፡- “አሁን እንደ ከዚህ ቀደሙ ለቴሌቪዥን ዲኮደር አልከፍልም፡፡ ለቤተሰቤ ውድ ልብስ መግዛትም አቁሚያለሁ፡፡”

ኮቪድ-19 ብዙ ነጋዴዎችን አኗኗራቸውን እንዲቀይሩ ቢያስገድዳቸውም ወይዘሮ ኪማሮ እራሷን ለመጠበቅ ጥንቃቄ እያደረገች ለቤተሰቧ ገቢ ለማግኘት የንግድ ሥራዋን ለመቀጠል ጠንክራ መሥራት እንደምጥቀጥል ትናገራለች፡፡ “ኮቪድ-19ን ለመከላከል ጭንብል አደርጋለሁ፣ እጄን በውሃና በሳሙና እታጠባለሁ፣ ሳኒታይዘርም እጠቀማለሁ፡፡”

“ይሄ ሁኔታ እስከ መቼ ድረስ እንደሚቀጥል አላውቅም፡፡ ደምበኞቼን ማታ ማታ እየደወልኩ ለነገ ትዛዝ በመቀበል የቦምቦሊኖ እና የሩዝ ቂጣ ሥራየን ለማረጋጋት አቅጃለሁ” ትላለች፡፡

ይህ ጽሁፍ በግሎባል አፌይርስ ካናዳ በኩል ከካናዳ መንግስት በተገኘ ድጋፍ ተዘጋጀ፡፡

Related

About Barza Wire

Barza Wire is a service of Farm Radio International.
This news service shares stories about rural communities in Africa. Our content is available for use by radio broadcasters. Sign up for the newsletter.


Contact Us

Farm Radio International
1404 Scott Street
Ottawa, Ontario
Canada, K1Y 4M8

Tel: 1.613.761.3650
Fax: 1.613.798.0990
Toll-Free: 1.888.773.7717
Email: barza.fm@farmradio.o

© 2025 Farm Radio International