Sisay Berihu | September 28, 2018
በፈጣን ሁሉን አውዳሚ ተምች ዙርያ ግንዛቤ ማሳደጊያ ላይ ያተኮረው ዓውደ ጥናት የሻይ ዕረፍት ሰዓቱ ደርሷል፡፡ አርሶ አደሮች በሻይ ቡና ሰዓታቸው የልምድ ልውውጥ ጨዋታቸውን ተያይዘውታል፡፡ በርሄ ተካ ከውይይቱ ወጣ በማለት ሻዩን እጁ ላይ ይዞ እንደቆመ በሃሳብ መመሰጡን ያስታውቃል፡፡ አንድ ባጣም አስፈላጊ ጉዳይ እያጠነጠነ ይመስላል፡፡
የ32 ዓመቱ አርሶ አደር ሁኔታው የተጨነቀ ይመስላል፡፡ አይኖቹ በእጁ ከያዘው የሻይ ኩባያ አሻግረው ሩቅ የሚያዩ ይመስላል፡፡ ከራሱ ጋር እየተወያየ ይመስላል፡፡ ጥልቅ ሃሳብ ላይ መሆኑን ማንም ከፊቱ ማንበብ ይችላል፡፡
አቶ ተካ የቦቆሎ ማሳው በፈጣን ሁሉን አውዳሚ ተምች በመወረሩ እጅግ እንዳስጨነቀው ይገልፃል፡፡ በመቀጠልም “የማሳዬ ጉዳይ እጅግ አሳስቦኛል፡፡ ወደዚህ ስልጠና ከመምጣቴ በፊት ማሳዬ በፈጣን ሁሉን አውዳሚ ተምች ተወሯል፡፡ በዚህ ሰዓት ተምቾቹ ማሳዬን ምን ያህል እንዳወደሙት እያሰብኩት ነው፡፡ ”
አቶ ተካ በኢትዮጵያ ብሄር ብሄረሰቦች ክልል ቤኪ በምትሰኝ መንደር ውስጥ ይኖራል፡፡ እርሱ “ፈጣን ሁሉን አውዳሚ ተምቾች ከባለፈው ዓመት የዝናብ ወቅት ጀምሮ ማሳዎቻችንን በአስከፊ ደረጃ እየጎዱት ነው፡፡”
በአካባቢው እንደሚገኙት አብዛኛዎቹ አርሶ አደሮች ሁሉ አቶ ተካም ፈጣን ሁሉን አውዳሚ ተምችን ለመከላከል ምንም ዓይነት ፀረ ተባይ አይጠቀምም፡፡ ተምቾችን ለመቆጣጠር ባህላዊውን ማለትም በእጅ መልቀምን እና መግደልን የመሳሰሉ ዘዴዎችን ነው የሚጠቀመው፡፡
ባለፈው ዓመት ፈጣን ሁሉን አውዳሚ ተምች ለቦቆሎ አርሶ አደሮች ቅዠት ሆኖ ከርሟል፡፡ ሆኖም ግን አቶ ተተካ የጋጠማቸው ጉዳት በቀጣይተምቹን ለመቆጣተር ምን ማድረግ እንዳለባቸው አስተምሯቸው ማለፉን ነው የሚገልፀው፡፡
በተጨማሪም “አርሶ አደሮቻችን ባለፈው ወቅት በተምቹ በተወረረ ጊዜ የሳት ራቶቹን እጮች በመሰብሰብ ለመግደል ችለዋል፡፡ ይህ ዘዴ የፈጣን ሁሉን አውዳሚ ተምች መስፋፋትን ከመግታት አኳያ ውጤታማ ሆኖ አግኝተነዋል፡፡ ” በማለት ይገልፃል፡፡
አለም ፀሀይ ዳርጌ የአካባቢው የግብርና ኤክቴንሽን ባለሙያ ናት፡፡ እርሷ “ከባለፈው ወቅት ጀምሮ አርሶ አደሮቻችን በእጅ የመልቀምን እና የመግደልን ዘዴ ሲተገብሩ ቆይተዋል፡፡ ምክንያቱም ዘዴው ውጤታማ ስለሆነ ነው፡፡ ባለፈው ዓመት ከ 20,000 ሄክታር በላይ የቦቆሎ ማሳዎች በፈጣን ሁሉን አውዳሚ ተምች ተጠቅተው የነበረ ሲሆን በዚሁ ዘዴ በመጠቀም ሙሉ በሙሉ ለማፅዳት ተችሏል፡፡ አርሶ አደሮቹ በዚህ ወቅትም ይህን ዘዴ እየተጠቀሙ ይገኛሉ፡፡”
አለምፀሀይ በተጨማሪም “ተስፋ አለው፤ እንደ ባለሙያ ውጤታማነቱን መመስከር እችላለሁ፡፡ ውጤታማ እስከሆነ ድረስም አርሶአደሮች ባህላዊ ዘዴዎችን ብቻ እንዲጠቀሙ አበረታታቸዋለሁ፡፡ ምክንያቱም ኬሚካሎችን መጠቀም የሚያስከትሉትን ችግር ላይገነዘቡ ይችላሉ፡፡ ”
ፀረ ተባይ ኬሚካሎች ተምቾችን ለመቆጣጠር ጠቃሚ ቢሆኑም የሰዎችን ጤና እና የአካባቢን ሊጎዱ ይችላሉ፡፡ በተጨማሪም እንደ ፈጣን ሁሉን አውዳሚ ያሉ ተምቾችን በተፈጥሮ ሚከላከሉ ዝርያዎችን ሊገድል ይችላል፡፡
አቶ አመንቲ ጫሊ በዩኤስ ኤ አይ ዲ ኢትዮጵያ የአገር አቀፍ ሰብል ምርት አስተባባሪ ሆኖ ያገለግላል፡፡ አቶ አመንቲ አርሶ አደሮች ፈጣን ሁሉን አውዳሚ ተምችን ለመቆጣጠር የተለያዩ ባህላዊ ዘዴዎችን መጠቀም እንዳለባቸው ይመክራል፡፡ እሱ እንደሚለው አብዛኛዎቹ አርሶ ሰደሮች በእጅ መልቀምን እና እጮችን እየገደሉ ለደሮዎቻቸው የመስጠት ባህላዊ ዘዴዎችን እየተገበሩ ይገኛሉ፡፡
አቶ አመንቲ የኢትዮጵያ አርሶ አደሮች ፈጣን ሁሉን አውዳሚ ተምችን ለመቆጣጠር አሻዋ ፣ ቃሪ ያ፣ የኒም ውጤቶችን እና ሳሙናን ጨምሮ በአካባቢያቸው የሚገኙ በርካታ መሳሪያዎች እንደሚጠቀሙም ገልጧል፡፡
“በኢትዮጵያ አካባቢያዊ ልምዶች ውጤታማ እየሆኑ ይገኛሉ፡፡ ሆኖም ግን ባህላዊዎቹ ዘዴዎችን መጠቀሙ የተሻለ አማራጭ ቢሆንም ባህላዊ ዘዴዎችን ብቻ መጠቀም በቂ ነው ማለት ግን አይደለም፡፡ ” ሲልም አመንቲ ያስረዳል፡፡ በተጨማሪ አርሶ አደሮች ፈጣን ሁሉን አውዳሚ ተምችን ለመቆጣጠር የተቀናጀ ዘዴን መጠቀም አስፈላጊ እንደሆነ አመንቲ ይገልፃል፡፡
አቶ ተካ ወደ አውደ ጥናቱ የሚመለስበት ሰዓት ደርሷል፡፡ እርሱ እንደሚለው ፈጣን ሁሉን አውዳሚ ተምች የሚያደርሰውን ጉዳት ለመቆጣጠር እንቅልፉን ቢያጣም የአካባቢው ባህላዊ ዘዴዎች መጠቀሙን ግን ይቀጥልበታል፡፡
ይህ በ ዩ ኤስ ኤ አይ ዲ ፊድ ዘ ፊውቸር ኢትዮጵያ ቫልዩ ቼይን አክቲቪቲ እንደ ፕሮጀክቱ አካል በመሆን ባደረገው ድጋፍ የተዘጋጀ ነው፡፡ “ICT-enabled Radio Programming on Fall Armyworm (FAWET).