ለአርሶ አደሮች የሚሆን ውጤታማ የዕቅድ አወጣጥ እና የአስቸኳይ ምላሽ ፕሮግራም አዘገጃጀት

| November 20, 2018

Download this story

አስቸኳይ ስንል ለአርሶ አደሮች ምንድነው ?

አስቸኳይ ስንል ድርቅ፣ ጎርፍ፣ የመሬት መንቀጥቀጥ፣ ከባድ መብረቅ፣ የጭቃ መንሸራተት፣ ወረርሽኝ፣ ግጭት እና ዓመፅ ፣ እና የተባይ መወረርን ጨምሮ ሌሎች የተለያዩ ጫፍ የደረሰ ተፈጥሮአዊ ወይም ሰው ሰራሽ አደገኛ ችግር ህይወትን የሚያወዛግብበት እና አስቸኳይ የእርዳታ ጥሪን የሚጠይቅ ሁኔታ ማለት ነው፡፡

የአርሶ አደሮች የአስቸኳይ ምላሽ ፕሮግራም ምንድነው ?

የአርሶ አደሮች የአስቸኳይ ጊዜ አደጋ ምላሽ ኮሚዩኒኬሽን እና የአደጋ ማረጋጋት ፕሮግራም አርሶ አደሮች ቀጥለው የተዘረዘሩትን እንዲተገብሩ የሚያግዝ ተግባር ነው፤
– ለተፈጠረው ችግር ዝግጁ መሆን፤
– በተቻለ መጠን በችግሩ ወቅት ችግሩን መቋቋም እና በቀጣይም የግብርና ልምዳቸውን በመለወጥ አደጋው በግብርናቸው እና በህይወታቸው ላይ ሊያደርስ የሚችለውን ጉዳት አነስተኛ እንዲሆን መዘጋጀት

የአስቸኳይ ጊዜ አደጋ ምላሽ ዝግጅቴ በምን መልኩ አድማጮቼን የበለጠ ሊያገለግልኝ ይችላል ?

– ሊከሰት እንደሚችል ስለተገመተው አደጋ ዝርዝር መረጃ አድማጮችን ያዘጋጃል፤
– አደጋው በሚከሰትበት ወቅት ሊቋቋሙባቸው ስለሚችሉባቸው አገልግሎቶች አስፈላጊ መረጃዎችን ለአድማጮች ይሰጣል፡፡
– አደጋው ከመከሰቱ በፊት፣ በተከሰተበት ሰዓት ፣እና በኋላ ማህበረሰቦች አደጋውን ስለሚቋቋሙበት ዘዴ እርስ በርስ መረጃ እንዲለዋወጡ ይረዳቸዋል፡፡
– ማህበረሰቦች በተመሳሳይ ችግር ሊደርስ የሚችለውን አደጋ እንዲቀንሱ የግብርና ተግባራትን ጨምሮ አስቀድመው፣ በችግሩ ወቅት ፣እና በኋላ ሊተገብሩዋቸው የሚገቡ ተግባራትን እንዲለዩ ይረዳቸዋል፡፡
– የአስቸኳይ አደጋ ድጋፍ እና ማረጋጋት ለተቋማት ጠቃሚ ግብረ መልስ ይሰጣል፡፡

http://scripts.farmradio.fm/am/radio-resource-packs/105-farm-radio-resource-pack/bh2-emergency-programming-amharic/