- Barza Wire - https://wire.farmradio.fm -

የሊዝ ሁግስ ሽልማት ለ ለስዋ የግብርና ፕሮግራም

ፋርም ሬድዮ ኢንተርናሽናል የሥርዓተ ፆታ እኩልነትን የሚመለከቱ እና በገጠር የሚኖሩ ሴቶችን ድምጽ ለማስተጋባት እና ለማጋራት እድሎችን የሚፈጥሩ የሬዲዮ ፕሮግራሞችን ለሚሰሩ ሬድዮ ጣቢያዎችና ጋዜጦኞች እውቅና ለመስጠት አዲስ ሽልማት አዘጋጅተዋል፡፡.ፋርም ሬድዮ ኢንተርናሽናል የሬድዮ ጣቢያዎች እና የፕሮግራም ዝግጅት ቡድኖችን ለ ሊዝ ሁግስ ሽልማት ለመወደደር ማመልከቻ እንዲያቀርቡ ይጋብዛል፡፡

ሊዝ ሁግስ የፋርም ሬድዮ ኢንተርናሽናል የቦርድ አባል የነበሩ ሲሆኑ የሬድዮ ስርጭት አድናቂና የስርአተ ጾታ እኩልነት አቀንቃኝ የነበሩ ናቸው፡፡የካናዳ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን ጋዜጠኛ የነበሩት እኝህ ሰው ፋርም ሬድዮ ኢንተርናሽናል ፣ፍትሃዊነት፤ ትክክለኛነት,፤ገለልተኛነት፤ታማኝነት እና ክብርን የሚያጎላ የ FAIR journalistic standards [1] ጋዜጣዊ ደረጃዎቹን እንዲጠቀም ረድተዉታል፡፡.

ከሰሃራ በታች በሚገኙ የአፍሪካ አገሮች ገጠራማ ቦታዎች ሴቶች ለግብርና, ለቤተሰብና ለማህበረሰቡ በጣም ወሳኝ ሚና ይጫወታሉ፤ ሆኖም ግን እጅግ የከፋ ድህነት፤ የተመጣጠነ ምግብ እጦት፤ጤና ማጣት፤እና ሀብቶችን የመቆጣጠር እድላቸው አናሳ ሆኖ ይገኛል፡፡ የሬዲዮ ፕሮግራሞች የሴቶችና የወንዶች ፍላጎቶች ለማሟላት ማገልገላቸው አስፈላጊ ነው፤በዚህ መንገድ ሴቶችም ሆኑ ወንዶች በ መረጃው ተጠቃሚ መሆን በመሆን ሁለቱም ለማህበረሰባቸው እድገት አስተዋፅኦ የማድረግ እድል ይኖራቸዋል፡፡ሴት አርሶአደሮችን እንዴት ማግልገል እንደሚቻል ከዚህ የፕሮግራም አሰራር መመሪያ ተጨማሪ መረጃ ያግኙ፣ Learn more about how to serve women farmers well (ሴት አርሶአደሮችን እንዴት በሚገባ ማገልገል ትችላላችሁ [2]).

ማንኛውም አፍሪካ ላይ የሚገኝ የሬዲዮ ጣቢያለ ሊዝ ሁግስ ለስዋ የግብርና ሬድዮ ሽልማት ማመልከት ይችላል፡፡ ለዚህ ውድድር ሲያመለክቱ ተወዳዳሪዎች ለውድድር የሚያቀርቡት ፕሮግራም የስርአተ ጾታ እኩልነትን ያገዘ ወይም እንዲሻሻል እድል የሰጠ ብለው የሚያሰቡትን ፕሮግራም ዝርዝር መረጃ ማቅረብ አለባቸው፡፡ ሬድዮ ጣቢያዎች በተለያዩ ፕሮግራሞች ከአንድ በላይ ማመልከቻ በማቅረብ መወዳደር ይችላሉ፡፡

አመልካቾች የተያያዘውን ፎርም ሞልተው እና የፕሮግራሙ ቅደም ተከተል የሚያሳይ ሰነድ ፤የፕሮግራሙን ቅጂ በ ኤምፒ 3 ማያያዝ አለባቸው፡፡. እነዚህ ሰነዶች በኢሜል radio@farmradio.org [3] ላይ መላክ አለባቸው፡፡ እባክዎን ርዕሰ-ጉዳይ : Liz Hughes Award for Her Farm Radio ይፃፉ

ማመልከቻዎች በእንግሊዝኛ, በፈረንሳይኛ, በአማርኛ, በስዋሂሊ እና በሃውሳ ቃንቃዎች መቅረብ ይችላሉ፡፡ ፕሮግራሙበስርጭቱ ቋንቋ ሊሆን ይችላል፡፡

ለማመልከት የመጨረሻው ቀን ይካቲት 9 ድረስ ነው፡፡

አሸናፊው ቡድን ለምርጥ ስራው እውቅና በመስጠት የምስክር ወረቀት እና 1,000 የካናዳ ዶላር ሽልማት ያገኛል፡፡

tLiz_Hughes_Award_Application_Form_AMharic [4]