- Barza Wire - https://wire.farmradio.fm -

የስርጭት ምንጮቻችንን እንዴት ማሻሻል እንዳለብን እንዲነግሩን መጠይቃችንን ይውሰዱ

የፋርም ሬድዮ ኢንተርናሽናል የስርጭት አጋር በመሆንዎ እናመሰግናለን፡፡ እርስዎ በ800 አፍሪካዊ ድርጅቶች የእኛን መረጃ እና ስልጠና ምንጮችን ከሚቀበሉ 2,000+ የሬድዮ አሰራጮች አንዱ ነዎት፡፡

ፋርም ሬድዮ ኢንተርናሽናል ለሬድዮ አሰራጮች በርካታ ምንጮችን ያዘጋጃል፡፡ እነዚህን በአራት አገልግሎቶች እናካፍላለን፡ ባርዛ ዋየር (Barza Wire) የፋርም ሬድዮ ምንጮች ይዘት፤ ኢ ዲስከሽንስ (eDiscussions) እና የኦንላይን የመማሪያ ሞጁሎቻችን፡፡ ሁሉንም የፋርም ሬድዮ ምንጮችን በ www.farmradio.fm [1] ማግኘት ይችላሉ፡፡

የስርጭት ኣጋር በመሆንዎ ምንጮቻችንን እንዴት እየተጠቀሙ እንደሆነ ፤ ምን ምን እንደተመቸዎት ፤ እና እንዴት ማሻሻል እንዳለብን ለማወቅ እንሻለን፡፡ እኛ ሁሌም በተለያዩ ርዕሶች ላይ አዳዲስ ምንጮችን በአዳዲስ ፎርማቶች እያዘጋጀን ነው፡፡ ስለዚህም የእርስዎን ግብአት እንሻለን፡፡

ይህ መጠይቅ 29 ጥያቄዎችን ይዟል ፤ መልሶችዎን ለሞሙላት ከ15-20 ደቂቃዎች ይወስድብዎታል፡፡

መጠይቁን ይውሰዱ https://survey.zohopublic.com/zs/zmB3ow?lang=nl [2]

የመጀመሪያዎቹ ጥቂት ጥያቄዎች መሰረታዊ ናቸው፡፡ ስለዚህ እባክዎን ስለ ራስዎ የተወሰነ መረጃ እንደሚያካፍሉን እርግጠኛ ይሁኑ፡፡

መጠይቁን የሚሞላ እያንዳንዱ ሰው የ $50 የሞባይል የአየር ሰዓት የሚያስገኘው እና ከሶስት ዕጣዎች ውስጥ የሚካተት ሆናል፡፡ ውድድሩ ውስጥ ለመግባት በመጠይቁያሉትን ጥያቄዎች በሙሉ መመለስ ይጠበቅበታል፡፡

መጠይቁ እስከ ታህሳስ 13 ፡ 2018 ድረስ ክፍት ይሆናል፡፡