ክትባት ላይ እምነት እንዲኖር በምናደርገው ዘመቻ ይቀላቀሉ

| March 18, 2022

Download this story

በኮቪድ-19 ምክንያት የሚከሰቱ ከባድ በሽታዎችን ለመከላከል እና ማህበረሰባችንን ጤናማ ለማድረግ ክትባቶች ወሳኝ ሚና አላቸው። ሆኖም በርካታ ሰዎች ኮቪድ-19 ክትባቶችን በሚመለከት ጥርጣሬ እንዳደረባቸው ነው ያሉት ጥያቄዎችም የፈጠሩባቸዋል። እንደ ስርጭት ባለሙያነትዎ እርስዎ  በማህበረሰብዎ ዘንድ ተዓማኒነት እና የተከበረ ድምጽ አለዎት። በፕሮግራሞችዎ አማካኝነት ሺዎች ለሚቆጠሩ ህዝብ ተደራሽ ነዎት። ድምጽዎን ለዚህ ወሳኝ ዓላማ ያውሉ! የኮቪድ-19 ክትባቶችን ለማስተዋወቅ፣ የአድማጮችዎን ጥያቄዎች ለመመለስ እና በማህበረሰብዎ ውስጥ ስላሉ ክትባቶች ተደራሽነት እና ውጤታማነት ላይ ጥሩ መረጃ ለማቅረብ የእኛን ዘመቻ ይቀላቀሉ።

ፋርም ሬዲዮ ኢንተርናሽናል በ16 አገሮች ውስጥ በሚገኙ የሬዲዮ አጋሮች ጋር በመተባበር ከግንቦት እስከ ነሃሴ 2014 ዓ.ም ባለው ጊዜ ውስጥ ክትባት ላይ እምነት የሚያሳድር ዘመቻ በአየር ለማዋል አቅዷል። እርስዎም በኮቪድ-19 ላይ ጥሩ መረጃን በአየር ሞገዶችዎ ላይ በማሰራጨት እንዲተባበሩን እንጠይቃለን።

የዘመቻዎቹ ይዘት አድማጮች ጋር በቀላሉ ሰርጸው የሚገቡ ዘለቄታ ያለቸው መልዕክቶችን እንዲሁም የመረጃ ፍላጎቶችን የሚፈቱ ቁልፍ ጭብጦችን የሚያካትቱትን በመምረጥ ከርስዎ ጋር አብረን የምንቀርጸው ነው የሚሆነው። የዘመቻው መልዕክቶች የሬዲዮ የአየር ሰአት ተመድቦላቸውና የቃለ መጠይቅ ክፍለ ጊዜዎችን ያካተቱ ፕሮግራሞች የሚተላለፉበት ይሆናል። በሬዲዮ ጣቢያዎ በሚተላለፉት መልእክቶች በኮል በተቻለ መጠን አዛውንቶችን፣ ወጣቶችን፣ ታዳጊዎችን አካተን በርካታ ሰዎችን መድረስ እንፈልጋለን። 

በዚህ ዘመቻ፣ ጣቢያዎ የሚከተሉትን ያከናውናል፦

  • ሃሰተኛ ዜናዎችን እና የተሳሳቱ መረጃዎችን ያጠራል
  • ከአድማጮች ስለ ኮቪድ-19 እና ስለክትባቶች በተደጋጋሚ የሚነሱ ጥያቄዎችን ይመልሳል
  • በማህበረሰቡ  ዘንድ ኮቪድ-19 ክትባትን ያስተዋውቃሉ
  • ሴቶችና እና ወንዶች ከኮቪድ-19 ጤንነታቸው ለመጠበቅ የሚረዳቸውን መረጃ ያቀርቡላቸዋል
  • እና ሌሎችም!

በኮቪድ-19 ላይ እርምጃ የምንወስድበት ጊዜ አሁን ነው። ዘመቻችንን ይቀላቀሉ። ዘመቻውን ለመቀላቀል ይህን ማስፈንጠሪያ ይጫኑ

ስለ ዘመቻው ዝርዝር መረጃዎች

ዘመቻውን ለመቀላቀል ከወሰኑ የሚከተሉትን ለመከወን ይስማማሉ ማለት ነው፦ በትንሹ 50 ደቂቃ ያህል የሚፈጅ ስለ ኮቪድ-19 ክትባት የሚዘግብ ፕሮግራም በየሳምንቱ ለማቅረብ፣ የህዝብ ጤና ጥበቃ እርምጃዎች (ጭምብል፣ አካላዊ መራራቅ፣ የእጅ መታጠብ፣ ወዘተ) እና ተዛማጅ የስርዓተ-ፆታ እኩልነት ጉዳዮችን  የሚዳስሱ ፕሮግራሞች ከ 10-12 ሳምንታት አየር ላይ ለማዋል። (የዘመቻው ትክክለኛ ጊዜ የሚወሰነው የዚህ ዘመቻ ተጽእኖን ከፍ ለማድረግ ከአካባቢው የጤና ባለስልጣናት ጋር በሚደረግ ውይይት ነው።) ይህ ዘመቻ በሬዲዮ ጣቢያዎ ቢያንስ 5 የተለያዩ ፕሮግራሞች ላይ የተላለፉ የቃለ መጠይቅ ክፍሎችን ያካትታል። ይህ ሲሆን በጣቢያዎ የሚተላለፉትን የስፖርት፣ ሙዚቃ፣ ፖለቲካ፣ የወጣቶች ፕሮግራም፣ የአርሶ አደሮች ፕሮግራም፣ የጤና ፕሮግራም እንዲሁም ሌሎች ፕሮግራሞችን ሊያካትት የሚችል ነው። ዘመቻው የእርስዎን የሬዲዮ አየር ሰአቶችን፣ ቅኝቶችን፣ የህዝብ አገልግሎት ማስታወቂያዎችን እና ሌሎች ቅርጸቶችን ሊይዝ የሚችል ነው። የዚህን ዘመቻ መልዕክቶችን በማህበራዊ ሚዲያዎችዎም እንደሚያጋሩ ተስፋ እናደርጋለን።

ከፋርም ሬዲዮ፣ በሃገርዎት ካሉ ኤሎች ሬዲዮዎች፣ ባለድርሻ አካላት ጋር፣ የጤና ኤጀንሲዎች፣ የማህበረሰብ ድርጅቶች እና የሴቶች ቡድኖች ጋራ በመሆን ለዚህ ዘመቻ ቅርጽ ለመስጠት በሚደረገው ክንውኖች ላይ የመሳተፉ እድል ይኖርዎታል።  

ከአድማጮችዎ አስተያየት የምንሰበስብበት መድረክ የሆነውን የኡሊዛ የህዝብ አስተያየት መሰብሰቢያ አየር ላይ የሚውልበትን ሰአት እንዲመድቡለትም  እንጠይቅዎታለን። ይህ ግብረ-መልስ ስለ አድማጭዎችዎ የመረጃ ፍላጎት እና ዘመቻው የፈጠረው ተጽእኖ ላይ የበለጠ እንድንረዳ ያደርገናል።

በዘመቻው የታቀፉ የሬዲዮ ስፖት አጠቃቀምን ጨምሮ በሬዲዮ ክህሎት እና ቅርፀቶች ላይ የሚያተኩር የስልጠና ክፍለ ጊዜዎችን እናቀርባለን። እነዚህ የስልጠና ክፍለ ጊዜዎች የእኛ የበይነ መረብ ላይ የሚገኙ የመማሪያ ሞጁሎች፣ የዋትስአፕ ቡድን እና ዙምን በመጠቀም የሚሰጡ ይሆናሉ። ስልጠናዎቹ የዘመቻ መልእክቶችን ለመስራት አስፈላጊውን መረጃ ለመሰብሰብ ከሚረዱ ከርዕሰ-ጉዳይ ባለሙያዎች ጋር ለመነጋገር እድል ይሰጣሉ። የሶስት-ሳምንት ጊዜ ማብቂያው ላይ ቡድንዎ ለዘመቻው ንድግ አስተዋፅዖ ማበርከቱ ይታያል። ይህ ስልጠና እና ንድፍ የሚጀምረው በሚያዝያ ወር ነው።

ፋርም ሬዲዮ ዘመቻውን ለማስተዋወቅ የሚረዱ የሬዲዮ ጽሁፎችን፣ ስፖት፣ የልምድ ማካፈያ ታሪኮችን እና ሌሎች ግብአቶችን ያዘጋጃል።

በአየር ላይ የዋሉትን ስፖት እና የፕሮግራም ክፎሉች የተመረጡ ቅጂዎችን በማጋራት ተሳትፎዎን እንዲያሳዩ ይጠየቃሉ። ቅጂዎችዎን የእኛ የኡሊዛ ሎግ መድረክ ላይ እንዲያኖሩ መግቢያ ይሰጥዎታል። በተጨማሪም ሁሉንም ዘመቻውን በሚመለከት አየር ላይ ያዋሉበትን ቀንና ሰአት ያካተተ ሪፖርት ማስገባት ይጠበቅቦታል።

ፋርም ሬዲዮ ኢንተርናሽናል በሚወስዱት እርምጃ ሁሉ እርስዎን ለመደገፍ ዝግጁ ይሆናል። የኔትዎርክ ኦፊሰሮቻችን በስልጠናው ወቅት እንዲሁም አየር ላይ ለማዋል በሚሰሩበት ወቅት ሁሉ  ግብዓቶችን ለማቅረብ፣ ለቃለ መጠይቅ የሚቀርብ ሰውን ለማገናኘት እኒሁም የርስዎን ጥያቄዎች ለመመለስ ከጎንዎ አይለዩም። 

በዘመቻው ውስጥ ሙሉ በሙሉ ለሚሳተፉ የሬዲዮ ጣቢያዎች ሁሉ መጠነኛ የክብር ሽልማትም በደስታ እናቀርባለን። በዘመቻው ለመሳተፍ ፈቃደኛ መሆንዎን ካመለከቱ የክብር ደብዳቤ አዘጋጅተን እንልክልዎታለን። ለመመዝገብ ይህን ማስፈንጠሪያ ይጫኑ፦  https://forms.gle/MJXVXqiqkxRuYu796