Paul-Miki Roamba | October 2, 2020
News Brief
በስልሳዎቹ የእድሜ ክልል የሚገኘው ኢሳካ ሊንጋኒ ጋዜጠኛና በፖለቲካዊ ጉዳዮች ላይ በሚይዛቸው አቋሞቹ በቡርኪና ፋሶ በጣም የታወቀ ሰው ነው፡፡ በተጨማሪም በኮቪድ-19 በመያዙ ይታወቃል፡፡ በበሽታው መያዙን ሚያዚያ ላይ ፖስት አድርጎ ነበር፡፡ ሊንጋኒ በሽታው ሊኖርበት እንደሚችል መጀመርያ የጠረጠረው ትኩሳት፣ ራስ ምታት፣ እንቅልፍ ማጣት እና ድካም ሲሰማው ነበር፡፡ ለኮቪድ-19 ቡድን ስልክ ደውሎ ከሶስት ቀን በኋላ ቤቱ መጥተው የአፍንጫ ጥራጊ ናሙና ወሰዱ፡፡ ከሁለት ቀን በኋላ ስልክ ደውለው ቫይረሱ እንደተገኘበት ነገሩት፡፡ በዚያው ቀን አንድ አምቡላንስ ደወሉን እያጮኸ ሊወስደው መጣ፡፡ ካገገመ በኋላ ሆስፒታል ውስጥ ስለነበረው የግብኣት እጥረት የተናገረ ሲሆን ለሆስፒታሉ ሠራተኞች ግን አድናቆቱን ገልጾ ነበር፡፡
በስልሳዎቹ የእድሜ ክልል የሚገኘው ኢሳካ ሊንጋኒ ጋዜጠኛና ዋጋዱጉ ውስጥ ኦፒኒዮ የተባለ ሳምንታዊ የህትመት ውጤት ዳይሬክተር ነው፡፡ በፖለቲካዊ ጉዳዮች ላይ በሚይዛቸው እና በቴሌቪዥን ክርክሮች ላይ በሚገልጻቸው አቋሞቹ በቡርኪና ፋሶ በጣም የታወቀ ሰው ነው፡፡ በተጨማሪም በኮቪድ-19 በመያዙ ይታወቃል፡፡
ሚያዚያ ላይ ነበር ቀልድ ነገር ጣል አድርጎ በፌስቡክ ፖስት ያደረገው፡፡ ከአቢጃን ሲመለስ በቫይረሱ እንደተያዘ ያምናል፡፡ ምናልባት አይሮፕላን ጣቢያ ውስጥ፡፡ ምናልባት አይሮፕላን ውስጥ፡፡
እስከ ሐምሌ 8 ድረስ በቡርኪናፋሶ 1,037 ሰዎች በቫይሱ ሲያዙ 53 ደግሞ ሞተው ነበር፡፡ ቢያንስ 880 ሰዎች ያገገሙ ሲሆን 102 ሕክምና ላይ ነበሩ፡፡
ሊንጋኒ በሽታው ሊኖርበት እንደሚችል መጀመርያ የጠረጠረው ትኩሳት፣ ራስ ምታት፣ እንቅልፍ ማጣት እና ድካም ሲሰማው ነበር፡፡ መጀመርያ ወባ የያዘው መስሎት ነበር፡፡ ኋላ ደግሞ ዴንጌ ትኩሳት መሰለው፡፡ ሁለቱም ምርመራ ግን ውጤቱ ኔጌቲቭ ነበር፡፡
ከዚያ የኪቪድ-19 ጉዳይን የሚከታተለውን ቡድን ለማግኘትና ለማረጋገጥ ወሰነ፡፡ “መጀመርያ ስደውልላቸው ኮቪድ-19 እንደሌለኝ ነግረውኝ ነበር፡፡ ግን ሕመሙ ስላልለቀቀኝ ደግሜ ደውዬ አጥብቄ ያዝኳቸው፡፡ የመጀመርያ ደረጃ ሕክምና ክትትል የሚያደርግልኝን ሐኪም እና ሌሎችንም ሰዎች እንዲያነጋግሩልኝ ጠየኳቸው” ይላል፡፡
ከሦስት ቀን በኋላ የሐኪሞች ቡድን ወደ ሊንጋኒ ቤት መጣ፡፡ “መሳጭ ቡድን ነው ይዘው የመጡት፡፡ መጀመርያ እራሳቸውን ከጀርም ካጸዱ በኋላ ከአፍንጫዬ ናሙና ለመውሰድ ሰውነታቸውን በሙሉ የሚሸፍን ለብስ ለበሱ” ሲል ያስታውሳል፡፡
ሁለት ቀን ከጠበቀ በኋላ ምርመራው ፖሲቲቭ እንደነበር በስልክ ተነገረው፡፡ “በዚያው ቀን ሌላ ቡድን አምቡላንስ ይዞ ደዎሉን እያጮኸ እኔን ወደ ሆስፒታልለመውሰድ መጣ፤ ጎረቤቶቼ ሁሉ ሰሙ፡፡”
ሆስፒታል ገብቶ የመጀመርያውን መዳኒት እየጠበቀ እያለ ማታ 12 ሰዓት አካባቢ ምግብ አቀረቡለት፡፡ ሳልታከም አልበላም አልኳቸው ይላል ሊንጋኒ፡፡ አራት ሰኣት አካባቢ ላይ ክሎሮኩዊን እና አዚትሮማይሲን ተሰጠው፡፡
ሆሰፒታል ለ10 ቀናት ቆዬ – አምስት ቀን ቴንጋንዶጎ ሆስፒታል አምስት ቀን ደግሞ ልዕልት ሳራ ክሊኒክ፡፡ ዋጋዱጉ ከተማ ኮቪድ-19 በሽተኞች የሚታከሙት በነዚህ ማእከላት ነው፡፡ በሆስፒታሎቹ ውስጥ ያለው የመሣርያ እና የቁሳቁስ አቅርቦት አሳዛኝ ነው ይላል፡፡ በሆስፒታሎቹ የኮቪድ-19 ስርጭትን ለመግታት የሚያስፈልጉት መሰረታዊ እርምጃዎች ሳሙና እና ሳኒታይዘር ባለመኖሩ መክንያት ሊተገበሩ አይችሉም ነበር፤ የጤና ሚኒስትሩ ታማሚዎችን በጎበኙበት ጊዜ ይህንን እውነታ ነግሯቸው ነበር፡፡
በሁለቱም ሆሰፒታሎች ውስጥ የነበሩት የሕክምና ቡድኖች ግን ታማሚዎችን ለመንከባከብ ያሳዩት የነበረው ትጋት ሊንጋኒን አስገርሞት ነበር፡፡
ሊንጋኒ ሆስፒታል ውስጥ በኮሮናቫይረስ ሲሰቃዩ ካያቸው ሌሎች ሰዎች ይልቅ እሱ በጣም እድለኛ እንደነበር ይናገራል፡፡ ሁለት ወይም ሦስት የሚሆኑ እንደሱ እድሚያቸው ስልሳዎቹ ውስጥ የነበሩ ታማሚዎች ነበር፤ ቀሪዎቹ ግን ወጣቶችና በኮሮናቫይረስ በጣም እየተሰቃዩ የነበሩ ሰዎች ናቸው፡፡
አሁን አገግሞ ወደ መደበኛ ሕይወቱ ከተመለሰ በኋላ ሊንጋኒ ጎረቤቶቹም ሆኑ የሥራ ባልደረቦቹ የተለየ ፊት እንዳላሳዩት ይናገራል፡፡ ካገገሙ በኋላ መገለል ያጋጠማቸው ሌሎች ሰዎች ግን ያውቃል – አምቡላንስ በሽተኞችን ፍለጋ ከመጣ ጀምሮ ጎረቤት አይጠይቃቸውም፡፡
ይህ ጽሑፍ ከካናዳ መንግስት “በቡርኪናፋሶ ወጣቶች መካከል ጤና፣ ጾታዊ እና ስነተዋልዶ መብቶችን እና ይህ ጽሁፍ በግሎባል አፌይርስ ካናዳ በኩል ከካናዳ መንግስት በተገኘ ድጋፍ ተዘጋጀ፡፡