The benefits of conservation agriculture: የዕቀባ እርሻ

| April 2, 2019

Download this story

ማስታወሻ ለአዘጋጁ

የእቀባ እርሻ የአፈርን ይዘት በመንከባከብ እና ለምነቱን በማሻሻል እንዲሁም ውሃን በማቀብ በአነስተኛ የምርት ወጪ ከፍተኛ ምርትን ማስገኘት ላይ ዓላማውን ያደረገ የግብርና አሰራር ዘዴ ነው፡፡

የዕቀባ እርሻ በሶስት መርሆች ወይም ልምዶች ላይ ይመሰረታል :

አፈሩ የመረበሽ ዕድሉ አነስተኛ ይሆን ዘንድ ደጋግሞ ማረስን ማስቀረት ወይም አነስተኛ እንዲሆን ማድረግ ፤
አፈሩ በቋሚነት እንዲሸፈን ማድረግ፤
ሰብልን ማቀያየር እና ማሰባጠር ፤
ይህ ፅሁፍ ደጋግሞ ማረስን በመቀነስ አርሶ አደሮችን እንዴት ተጠቃሚ ማድረግ እንደሚቻል እና የአፈር መሸርሸርንም መቀነስ የሚቻልበትን ሁኔታ ላይ ትኩረቱን ያደርጋል፡፡
ፅሁፉ ቃለ መጠይቆች ላይ የተመሰረተ ነው ፡፡ በአካባቢሽ በተመሳሳይ ርዕሰ ጉዳይ ላይ ጥናት ለማድረግ ወይም ፅሁፍ ለማዘጋጀት እንደ መነሻ መጠቀም ትችያለሽ ፡፡ አልያም ይህን ፅሁፍ ለጣቢያሽ በሚሆን መልኩ ተናጋሪዎቹን ወክለው የሚያነቡ ባለሙያዎች ተጠቅመሽ በማስነበብ ማዘጋጀት ትችያለሽ፡፡

በተጨማሪም ይህን ፅሁፍ እንደ ምርምር ማቴሪያል ወይም በእቀባ እርሻ አስፈላጊነት ዙርያ የራስሽን ፕሮግራም ለማዘጋጀት እንደ መነሻ መጠቀም ትችያለሽ ፡፡ በሚከተሉት ርዕሰ ጉዳዮች ዙርያ አርሶ አደሮችን ፤ የግብርና ሰራተኞችን ፤ እና ሌሎች ባለሙያዎችን መጠየቅ ትችያለሽ፡-

በአካባቢዎ ምን አይነት የግብርና ችግሮችን ነው በዕቀባ እርሻ አማካኝነት መፍታት የሚቻለው?
ቶሎ ቶሎ ደጋግሞ ማረስ የአፈር ጥራትን እና ስነ ቅርፅን በምን መልኩ ሊጎዳ ይችላል ?
አነስተኛ የእርሻ ድግግሞሽን የሚከተሉ አርሶ አደሮችን አረምን እና ተባዮችን በምን መልኩ ይቆጣጠራሉ ?
አርሶ አደሮችን እና ሌሎች ባለሙያዎችን በቀጥታ ከማናገር ባሻገር የሚከተሉትን ጥያቄዎች ስልክ በመደወል ወይም በፅሁፍ መልዕክት ለሚዘጋጅ ፕሮግራም እንደ መነሻ መጠቀም ትችያለሽ፡፡

ይህን ፕሮግራም ከእነ መግቢያ ፣ መሸጋገሪያ፣ እና መውጪያ ድምፆች ጋር በአጠቃላይ የ 20 ደቂቃ ርዝማኔ ይኖረዋል፡፡

http://scripts.farmradio.fm/am/radio-resource-packs/110-farm-radio-resource-pack/benefits-of-conservation-agriculture-amharic/